"Please wait"
እባክወ በትዕግስት ይጠብቁ!
የኢንተርኔት ድክመት ነው!
🤝 ነፃና ገለልተኝነት
🤝 አገልጋይነትና ተባባሪነት
🤝 እውነተኛነትና ልህቀት
🤝 ቅልጥፍና እና ውጤታማነት
🤝 ሙያዊ ብቃት
🤝 ግልፅነትና ተጠያቂነት
🤝 ግብ ተኮር
🤝 ቅንጅታዊ አሰራር
ተልዕኮውን በብቃት መፈጸም የሚችል በስነ-ምግባሩ የተመሰገነ ሲቪል ስርቪስ በ2022 ዓ.ም በክልሉ ተገንብቶ ማየት፤
በመንግስት ተቋማት ያለውን አደረጃጀትና አሠራር ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ፍትሃዊ በማድረግ የሰው ሃብቱን በማልማትና በማስተዳደር እንዲሁም በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ ሥርዓት በመዘርጋት የመንግስትን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በብቃት መፈፀም የሚችል ሲቪል ሰርቪስ መፍጠር፡፡
👉የክልሉን ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ኃብት ልማት የሚመለከቱ ፖሊሲዎችን፣ስትራቴጅዎችን እና ሕጎችን ያመነጫል፣ የወጡ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂና ህጎችን ሥራ ላይ ያውላል፣ ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ አስፈላጊውን ማስተካከያ ያደርጋል፤
👉የክልሉን ሲቪል ሰርቪስ የደመወዝ ስኬል፣ ልዩ ልዩ አበሎችንና ጥቅማ ጥቅሞችን አጥንቶ ያስወስናል፣ ሲወሰን ተግባራዊ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
👉የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን አስመልክቶ ፖሊሲዎችንና ሕጎችን ያመነጫል፣ ከክልል ጀምሮ እስከ ታችኛው የመንግስት መዋቅር በሚገኙ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣ አፈፃፀምን የሚያሻሽል የማበረታቻ ሥርዓት ይዘረጋል፣ ጉድለቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፣ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
👉ለክልሉ ዘላቂ ዕድገት አስተዋፅዖ ሊያደርጉ የሚችሉ የተቋማት ሪፎርም ሥራዎችን በማጥናት ለሚመለከተው አካል የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ይከታተላል፣ ድጋፍ ያደርጋል፤
👉ተቋማት በአሠራር እንዲጠነክሩ እና በተገቢ መንገድ ሥራዎችን እንዲያከናውኑ ያግዛል፣ ከተቋማት በተናጠል የሚቀርቡ አስፈላጊ የሥራ መደቦችን ይፈቅዳል፤
👉የተቋማት ዓላማ ስኬታማ ለማድረግ የሚያስፈልገውን አደረጃጀትና የሰው ኃይል ፍላጎት ያጠናል፣ ይወስናል፣ ከተቋማት በተናጠል የሚቀርቡ የሥራ መደቦች ላይ በሕጉ መሰረት ውሳኔ ይሰጣል፤
👉የሥራ ምዘና እና ደረጃ አወሳሰን ጥናት ያካሂዳል፣ የስራ መደቦችን ስራ ዝርዝር ያዘጋጃል፣ ይመዝናል፣ ተግባራዊ ስለመሆኑ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
👉በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ላይ የለውጥ ፕሮግራሞችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ ክትትል፣ ግምገማና ድጋፍ ያካሂዳል፤
👉በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ተቋማት የመንግሥት ሰራተኞች የሥራ አፈፃፀም ምዘና ሥርዓት ይዘረጋል፣ የመንግሥት ሰራተኞችን ብቃትና ውጤታማነት በየጊዜው ይገመግማል፣ ይመዝናል፣ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ የመንግሥት ሰራተኞች ብቃትና ውጤታማነት የሚገነባበትን ሥልት ይነድፋል፣ ሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፤
👉ለክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ተቋማት የመንግሥት ሠራተኞች የቅጥር፣ የምደባ፣ የዝውውር፣ የደረጃ እድገት አሰራር ፍትሃዊ፣ ግልጽ እና ብቃትን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ያደርጋል፣ ያረጋግጣል፣ ሕግንና መርህን ተከትሎ እንዲፈፀም ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣ የስምሪት ጉድለት ሲፈጸም የእርምት እርምጃ ይወስዳል፣ያስወስዳል፤
👉በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ውስጥ በመንግሥት ሠራተኞች የሚቀርቡ ይግባኞች በአስተዳደር ፍርድ ቤቱ አማካኝነት መርምሮና አጣርቶ በፍሬ ነገር ደረጃ ውሳኔ ይሰጣል፤
👉በሁሉም ተቋማት ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓት እንዲዘረጋ በማድረግ የክልሉን የመንግሥት ሠራተኞች ዝርዝር መረጃ መዝግቦ ይይዛል፣ ስታቲስቲካዊ መረጃዎችን ያጠናቅራል፤
👉በሲቪል ሰርቪስ ዘመናዊ የተሟላ ሰብአዊ ሀብት አመራር እንዲኖር በሠራተኞች ላይ የሚታዩ የአቅም ክፍተቶችን በጥናት ይለያል፣ በትምህርትና ስልጠና ያበቃል፣ የሰው ሀብት ልማቱን በተማከለ መልኩ ለመምራት የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊ እንዲሆን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ ይወስዳል፤
👉የሲቪል ሰርቫንቱን የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ሥልጠና የሚፈፀምበትን የአሰራር መመሪያ በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ስራ ላይ ያውላል፣ ይከታተላል፣
👉የሲቪል ሰርቪሱን አቅም ለመገንባት አስፈላጊ የሆኑ የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት እንዲሁም የብቃት ምዘና ማዕከላት እንዲቋቋሙ ለክልሉ መንግሥት ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል፣ ይደግፋል፣ ያስተዳድራል፣
👉የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ ጥናት ያደርጋል፣ ህዝባዊ መድረኮችን እና ወርክ ሾፖችን ያዘጋጃል፣ ውጤታማነቱን ያረጋግጣል፤
👉የክልሉ መንግሥት ሠራተኞች ሥነ ምግባር ለማሻሻል የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
👉ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ እና የቅሬታ ማስተናገጃ ሥርዓት መዘርጋታቸውን እና ሥራ ላይ ማዋላቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣ ጉድለት ሲያጋጥም የእርምት እርምጃ ይወስዳል፣ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
👉የመንግሥት ሠራተኛ የጡረታ ዕድሜው ሞልቶ ነገር ግን በሚሰራበት ተቋም ለተጨማሪ ጊዜ እንዲያገለግል የተቋም ሃላፊ ጥያቄ ሲያቀርብ በህጉ መሰረት ውሳኔ ይሰጣል፤
👉ልዩ የሥራ ባህሪ ወይም የሥራ ክብደት ያላቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ላይ ተመስርቶ ልዩ ቅጥር እና ጥቅማጥቅም እንዲፈቀድ ጥያቄ ሲቀርብለት ጉዳዩን በጥልቀት መርምሮ ለክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፤
👉ውድድርን መሰረት ያደረገ ነፃ፣ ገለልተኛ፣ አካታችነትን ያረጋገጠ እና የክልሉን ብዝሀነት የሚያስተናግድ የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፤
👉ቀልጣፋና ውጤታማ የመንግስት አገልግሎት እንዲኖር ለማድረግ ለሲቪል ሰርቫንቱ የስልጠና መርሃ ግብሮችን በመንደፍ ክህሎታቸውን፣ እውቀታቸውን እና ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ ያደርጋል፣ ሙያዊ እድገት እና ውጤታማ የመንግስት አስተዳደርን እንዲረጋገጥ ይሰራል፤
👉የክልሉን እቅድ ለማሳካት የሰው ኃይል ፍላጎትን በመተንተንና የመጭውን ፍላጎት በመተንበይ ሲቪል ሰርቪሱ በቂ እና የሰለጠነ የሰው ሃይል መሟላቱን ያረጋግጣል፣ ለተግባራዊነቱም ይሰራል፤
👉ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን የሲቪል ሰርቪስ አገልጋይነትን ለማጠናከር፣ ተነሳሽነቶችን ለማሳደግ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ እና የመንግስት አቀፍ ስትራቴጂዎችን ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል፤
👉ቴክኖሎጅን በመጠቀም ከተገልጋይ እና ከሰራተኛ እርካታ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በመሰብሰብ እና በመተንተን ፖሊሲ ለመቅረፅ እና አሰራሮችን ለማሻሻል የሚያስችሉ ጥናት ያደርጋል፣ በግኝቱ መሠረት የማሻሻያ ሃሳቦች በመቅረፅ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
👉የሲቪል ሰርቪሱን ባህርያት ከተቋማት ፖሊሲ፣ ራዕይ፣ ዕሴቶች እና ግቦች ጋር እንዲጣጣም፣ ሰራተኞች ምቾት ተሰምቷቸው ስራን በብቃት እንዲሰሩና ሕዝብን በቅንነት እንዲያገለግሉ የሚያደርግ ምቹ የሥራ ቦታና የስራ አውድ እንዲፈጠር ይሠራል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ወሎ ዞን የሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ኃላፊ
የአቤቱታና ቅሬታ ማስተናገጃ ባለሙያ
የሪፎርም ድጋፍ ክትትል ቡድን መሪ
......
የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ የእቅድ በጀት ዝግጅትና ክትትል ግምገማ ባለሙያ