ሁለተኛ ዙር የሰሜን ወሎ ዞን መንግስት ሰራተኛ ትምህርት ማስሪጃ የማጣራት ስራ ሊጀመር ነው ። ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን )
20-04-2026 08:57amሁለተኛ ዙር የሰሜን ወሎ ዞን መንግስት ሰራተኛ ትምህርት ማስሪጃ የማጣራት ስራ ሊጀመር ነው ።
ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን )
ሁለተኛ ዙር የመንግስት ሰራተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ስራ ሊጀመር መሆኑን የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ሃላፊ ወ/ሪት ሙሉ አዲሴ ገለፁ።
የመምሪያ ሃላፊዋ እንደገለፁት በየደረጃው ያሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት እንደ-ሀገር ከተቀመጡ ፖሊሲወች አንዱ በየደረጃው ያለውን አመራርና መ/ሰራተኛ የትምህርት ማስረጃ ማጣራት ስራ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ተናግረዋል ።
የዜጎች አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ብቃት ባላቸው ሰራተኞች አገልግሎት ለመስጠት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ማጣራት ስራ የተጀመረው አንዱ የሪፎርም አካል ነው ብለዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ ሰው ሃብትወ ልማት መምሪያ ሃላፊ ወ/ሪት ሙሉ አዲሴ እንደተናገሩት የሀሰተኛ የትምህርት መረጃ የማጣራት ስራው በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

