👤👤Staff

"Please wait"
እባክወ በትዕግስት ይጠብቁ!
የኢንተርኔት ድክመት ነው!

የሰሜን ወሎ የዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ለወረዳና ለከተማ አስተዳደር የተቋማት አመራርንና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

23-04-2026 12:33pm

የሰሜን ወሎ የዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ለወረዳና ለከተማ አስተዳደር የተቋማት አመራርንና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡
ወልድያ የካቲት 26/2017 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን) የዞኑ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ የተቋሙ ማናጅመንት አባላትና ባለሙያዎች ጨምሮ ለወረዳና ከተማ አስተዳደር የተቋማት አመራርንና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥተዋል፡፡
ስልጠናዉን የሰጡት የዞኑ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ የሪፎርም ድጋፍና ክትትል ቡድን መሪ አቶ ተስፋዉ ዘገየ እና የሪፎርም ድጋፍና ክትትል ባለሙያ አቶ ይበልጣል አለማዬህ በጋራ በመሆን
በለውጥ አሰራርና አደረጃጀት ፣BSC እቅድ አስተቃቀድና እንዲሁም ውጤት አሞላልና ሰኔ/2016 ዓ.ም ተሻሽሎ በወጣው መመሪያ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የስልጠናዉ ተሳታፊዎች ሰልጠናዉ BSC እቅድ አስተቃቀድና ውጤት አሞላል የነበረብን የግልፀኝነት ችግር እንዲቀረፍ እንዳደረገና እንዲሁም በመመሪያዎቹ ዙሪያ በዚህ መልኩ በጋራ ግንዛቤ መፈጠሩ በወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር የሚታዩ የአፈፃፀም ልዩነቶች እንዲቀራረብ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይም አዳዲስ በሚወጡ መመሪያዎችና ደንቦች ላይ በዚህ መልኩ ግንዛቤ ቢፈጠር ከዞን እስከ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የሚናበበ፣ ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ እንደሚኖር ተሳታፊዎቹ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡
የዞኑ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉ አዲሴ የዚህ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ዋና ዓለማ በደጋፍና ክትትላችን፣ በአመራርና በሰራተኛው የታዩትን የአሰራር ክፍተቶች ለመሙላት ያለመ ነዉ ብለዋል፡፡
ከዚህ ስልጠና በኋላ አመራራችንና ባለሙያዎች መነሳሳት ተፈጥሮላቸዉ በእዉቀት ላይ ተመስርተዉ ወቅቱ የሚጠይቀውን አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ እንደሚያደርገዉና ቀጣይም በሚመጡ አዳዲስ አሰራሮችና መመሪያዎች ተከታታይነት ያለው ስልጠና ይሰጣልም ብለዋል፡፡
በመድረኩ ማጠቃለያም በመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት የተሸለ አፈፃፀም ለነበራቸዉ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች፣ ለተቋሙ ፈፃሚዎችና ቡድኖች የዕዉቅናና የሽልማት ስነ ስርዓት ተካሄዷል፡፡

loading

ይህ መረጃ 28 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇   ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form