👤👤Staff

"Please wait"
እባክወ በትዕግስት ይጠብቁ!
የኢንተርኔት ድክመት ነው!

የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ ሰው ሃብት ልማት መምሪያ የዞን መምሪያዎችን የ6 ወር የሪፎርም ምዘና አካሄደ ።

20-04-2026 08:53am

የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ ሰው ሃብት ልማት መምሪያ የዞን መምሪያዎችን የ6 ወር የሪፎርም ምዘና አካሄደ ።
የካቲት 04/2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን )የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰረቪስ ሰው ሃብት ልማት መምሪያ የዞን መምሪያዎች በ6 ወሩ ያከናወኑአቸውን የሪፎርም ተግባራት ምዘና ማካሄዱን የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ሃላፊ ወ/ሪት ሙሉ አዲሴ አሳወቁ።
የሪፎርም ተግባራት በየጊዜው እየተገመገሙና እየተመዘኑ መሄዳቸው ለተግባር አፈፃፀም የጎላ ሚና ከመኖራቸው በተጨማሪ ተግባራት በተቀመጠላቸው ጊዜ እንዲፈፀሙ ይረዳሉ ብለዋል።
ወ/ሪት ሙሉ አያይዘውም የዞን መምሪያዎች የሪፎርም ተግባራት በተቀመጠው የመመዘኛ መስፈርት መሰረት መዛኝ ኮሚቴዎቹ በአግባቡ የመዘኑት ሲሆን አብዛኛው መምሪያም ከሪፎርም ተግባር አኳያ መሻሻል የታየበት መሆኑን ገልፀው ቀጣይም አመራሩ ለሪፎርም ተግባር ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል ።

loading

ይህ መረጃ 27 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇   ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form