የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ
28-04-2026 12:21pmየሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ጠቅላላ ሰራተኛ የመንግስት ሰራተኞች ፐርሶኔል መረጃ ማጥራትና ማረጋጥ (ቆጠራ)ማስፈጸሚያ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
በሰሜን ወሎ ዞን የመንግስት ሰራተኞችን መረጃ በዲጂታል የማደራጀትና የማረጋገጥ ስራ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በመምሪያው ጠቅላላ ሰራተኞች ተካሄደ።
ወልዲያ ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ)
በሰሜን ወሎ ዞን ሀገራዊ የመንግስት ሰራተኞች መረጃ ማረጋገጥን (Civil Service Census) አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ሃላፊ ወ/ሪት ሙሉ አዲሴ የመነሻ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ የዚህ ተግባር ዋና ግብ የተበታተነ የሰራተኛ መረጃ አያያዝን ወደ አንድ ማዕከላዊ ቋት (Digital Database) በማምጣት አገልግሎቱን ከተገልጋዩ ፍላጎት ጋር ማጣጣም ነው።
በመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞችን አጠቃላይ መረጃ በዲጂታል ስርዓት ለመመዝገብ የሚከናወነው የመረጃ ትክክለኛነትን የማረጋገጥ ስራ በመጪው ሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚጀመር ሃላፊዋ ማመላከት ችለዋል።
ይህ የቆጠራና የመረጃ ማጥራት ስራ መንግስት አምኖበት አቅጣጫ ያስቀመጠበት በመሆኑ፣ በየደረጃው የሚገኝ አመራርና የመንግስት ሰራተኛ ስራውን ከተሳሳቱ አረዳዶች ወጥቶ በትክክለኛው ግንዛቤ ሊረዳው ይገባል ብለዋል።
ሰራተኛው አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን ቀድሞ በማሟላትና ለቆጠራው ራሱን ዝግጁ በማድረግ በቆጠራው ቀን አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ መልዕክት ተላልፏል። አክለውም የስልጠና ዓላማ የመረጃ ማጥራቱ ዋና አላማ ዲጂታል ሲቪል ሰርቪስን እውን ለማድረግ ያለውን የሰው ሃይል ቆጥሮ፣ በስራ ልምድና በሌሎች መመዘኛዎች ተለይቶ የጠራ መረጃ እንዲኖር ማስቻል መሆኑን አስገንዝበዋል።
መረጃው በጥራት እንዲጠናቀርና ስራው በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ ተጠናቆ ውጤት እንዲመጣ ሁሉም አመራርና ባለሙያ እኩል ሃላፊነት መውሰድ እንዳለበት አሳስበዋል።
ወልዲያ/2018ዓ/ም

.jpg)
.jpg)
