👤👤Staff

"Please wait"
እባክወ በትዕግስት ይጠብቁ!
የኢንተርኔት ድክመት ነው!

በሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ የአካል ምልከታና ድጋፍ ተካሄደ።

23-04-2026 11:47am

በሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ የአካል ምልከታና ድጋፍ ተካሄደ።
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ቢሮ በከፍተኛ አመራሮች የተመራ ልኡክ ቡድን በሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ በመገኘት ሰሞኑን ሲያካሂድ የነበረውን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ፣ ድጋፍና ክትትል እንዲሁም የአካል ምልከታ የነበረውን መርሀ-ግብር በማጠናቀቅ የመውጫ ግምገማ አከናውኗል።
የድጋፍ ቡድኑ አጠቃላይ የነበረውን ምልከታ ግብረ-መልስ በጥንካሬና በድክመት ሪፖርት በማቅረብ ጥንካሬወቹ ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የታዩት ድክመትች ደግሞ በቀጣይ እንዲስተካከሉ የመፍትሄ አቅጣጫ በማመላከትና የቀጣይ የስራ መመሪያ በመስጠት ቆይታቸውን አጠናቀዋል።
በቀጣይ የመንግስት አስተዳደርና አገልግሎት ሪፎርም ስራወችና የሰው ሀይል ማጠናከር በተሟላ አግባብ ውጤታማ እንዲሆን በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና መላ መንግስት ሰራተኞች የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ጠንከር ያለ መልእክት አስተላልፈዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ሙያተኞች ለተደረገልን ሙያዊ ድጋፍና ለተሰጠን ገላጭና አስተማሪ ግብረ-መልስ ከልብ እያመሰገን በቀጣይም ድጋፍና ክትትሉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

loading

loading

loading

loading

loading

loading

loading

ይህ መረጃ 43 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇   ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form