የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የ6 ወራት የለውጥ ተግባራት አፈፃፀምን ገመገመ።
20-04-2026 08:44amየሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የ6 ወራት የለውጥ ተግባራት አፈፃፀምን ገመገመ።
ወልድያ:- መጋቢት 07/2018 ዓ/ም (ሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን) የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የ6 ወራት የለውጥ ተግባራት አፈፃፀምን ከዞን አመራሮችና የቡድን መሪዎች ጋር ገምግሟል።
በግምገማ መድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት የታቀዱ የለውጥ ስራዎች፣ የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻሎች እና የሰው ሃብት ልማት ስራዎች ውጤታማነት ያመላከተ ውይይት ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የተገኝቱ የሰሜን ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት ንጋቱ ተቋማት ከቆየውና አሰልቺ ከሆነ አሰራር ወጥተው ለህዝቡ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ መስጠት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
ምክትል አስተዳዳሪው አክለውም የመንግስት ተቋማት ለአገልግሎት ፈላጊው ማህበረሰብ ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ፍትሃዊ አገልግሎት በመስጠት የህዝብን እርካታ ማረጋገጥ የቀጣይ ጊዜ ዋነኛ ትኩረት ሊሆን እንደሚገባም ገልጸዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ሃላፊ ሙሉ አዲሴ በበኩላቸው፣ የሪፎርሙ ዋና ዓላማ በተቋማት ውስጥ የሚታዩ የአገልግሎት መጓተቶችንና የቢሮክራሲ ማነቆዎችን መፍታት መሆኑን በመግለፅ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛው በስነ-ምግባር የታነፀና አገልጋይነትን በተግባር የሚያሳይ እንዲሆን መምሪያው አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
የለውጥ ተግባራት የመደበኛ ስራዎቻችን ማሳለጫ በማድረግ አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ፈጣን፣ ግልጽ እና ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባም ኃላፊዋ ገልፀዋል።
በመድረኩ ላይ የተቋማት የሪፎርም አተገባበርና የአገልግሎት አሰጣጥ የተሰሩ ስራዎች በአካል ድጋፍ በማድረግ የተገኙ ግኝቶች ለመድረኩ ተሳታፊዎች በሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።












