የመንግሥት ሠራተኞች ለመንግሥትና ለሕዝብ ድልድይ በመሆን የፖሊሲና ስትራቴጂዎችን የማስፈጸም ሚናቸው አይተኬ መሆኑን አቶ ከድር አስገንዝበዋል በመሆኑም ለሕ
19-04-2026 15:10pm የአገር ግንባታ ጥንካሬ በመንግሥት ሠራተኛው ብቃትና ታማኝነት ላይ የተመሠረተ ነው" - አቶ ከድር ሙስጦፋ
ወልድያ — መጋቢት 01/2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን) የአንድ አገር የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የፖለቲካ መረጋጋትና የማህበራዊ ፍትህ መረጋገጥ ዋነኛው መሠረት የመንግሥት ሠራተኛው ብቃትና ታማኝነት መሆኑ ተገለፀ።
ይህ የተገለጠው የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ከተቋሙ ሠራተኞች ጋር በአዲሱ የተሻሻለ አዋጅ ዙሪያ በሚያካሂደው የሥልጠና መድረክ ላይ ነው።
በሥልጠናው መድረክ ላይ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ የሰሜን ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከድር ሙስጦፉ እንደተናገሩት፣ አዲሱ የሲቪል ሰርቪስ አዋጅ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን አደረጃጀትና የሰው ኃይል አስተዳደርን ለማዘመን ታሳቢ ያደረገ ነው ተብለዋል።
ኃላፊው አክለውም ማንኛውም ቅጥር፣ ዕድገትና ሹመት ከዝምድና ወይም ከፖለቲካ ወገንተኝነት የጸዳ መሆን አለበት ብለዋል።
አሠራሩ በዕውቀት፣ በክህሎትና በሥራ አፈጻጸም ላይ ብቻ የተመሠረተ መሆን ይኖርበታል ያሉት ኃላፊው ሠራተኛው በዕውቀትና በሥነ-ምግባር ሲታነጽ የአገር ግንባታው በዚያው ልክ ይጠነክራልም ብለዋል።
የመንግሥት ሠራተኞች ለመንግሥትና ለሕዝብ ድልድይ በመሆን የፖሊሲና ስትራቴጂዎችን የማስፈጸም ሚናቸው አይተኬ መሆኑን አቶ ከድር አስገንዝበዋል በመሆኑም ለሕዝብ የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት ውጤታማ ሥራ ሊከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሪት ሙሉ አዲሴ በበኩላቸው፣ መምሪያው ለተገልጋዮች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠርና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
አዲሱ አዋጅ የሞሰብ አንድ ማዕከል አገልግሎት እና የሕፃናት ማቆያዎችን በማደራጀት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት፣ በየደረጃው የሚታዩ ብልሹ አሠራሮችን ለማስወገድ ፋይዳዎች እንደሚኖሩትም ኃላፊዋ ጠቁመዋል፦
የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን ዘመናዊ ለማድረግ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ተብሏል።
በዚህ የሥልጠና መድረክ ላይ በዞኑ የሚገኙ ሁሉም የመምሪያ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

