ወቅቱ የሚጠይቀውን የዘመነ አገልግሎት ለመስጠት የሰው ሀይሉ ራሱን በቴክኖሎጂ እንዲያለማና ለመጪው የዲጂታላይዜሽን ዘመን ራሱን ማሰልጠን እንዳለበት የሰሜን ወሎ
NWCIV:01-11-2025 15:22pmወቅቱ የሚጠይቀውን የዘመነ አገልግሎት ለመስጠት የሰው ሀይሉ ራሱን በቴክኖሎጂ እንዲያለማና ለመጪው የዲጂታላይዜሽን ዘመን ራሱን ማሰልጠን እንዳለበት የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ አስታወቀ፡፡ ጥቅምት 11/2018 ዓ/ም(ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን ) የሰ/ወ/ዞ/ሲ/ሰ/የሰ/ሀ/ል መምሪያ የ2018 ዓ.ም በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት ተግባር አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል፡፡ በመጀመርያው ሩብ አመት ሊሰሩ ከታቀዱት ውስጥ በጥንካሬ የፈጸምናቸውን ጠብቀን በማስቀጠል በድክመት አቅደን ያልፈጸምናቸውን ለይተን የቀጣይ የእቅድ አካል አድርገን በፍጥነት በማረም ለውጥ ማምጣት አለብን ሲሉ የመምሪያው ሃላፊ ወይዘሮ ሙሉ አዲሴ ተናግረዋል፡፡ ሃላፊዋ በሩብ አመቱ ሊከናወኑ ከታቀዱት ተግባራት ውስጥ በርካታ ተግባራት በተሻለ አፈጻጸም የተከናወኑ ሲሆን በተለይ ከለውጥ ተግባራት ጋር በተያያዘ ወደ ጎን የምናስተዳድራቸው ተቋማት በየደረጃው ያለ ሲቪል ሰርቪስ ተቋም በተቀመጠው አሰራር በተደረገው ወጥ የሆነ ድጋፍና ክትትል እነዚህን ተግባራት የመደበኛ ተግባር ማሳለጫ መሆናቸውን አምኖ በመተግበርና በማስተግበር በኩል የተሰራው ስራ የመጣው የአመለካከት ለውጥ በማህበራዊ በኢኮኖሚና በመልካም አስተዳደር ለተገኘው ስኬት የጎላ አስተዋጽኦ የተመዘገበበት ነው ብለዋል፡፡ የሰው ሀይሉ የመጣውን ሀገራዊ ሪፎርም በውል ተረድቶ የመፈጸም አቅሙም እንዲያድግ የሰው ሀይሉ በእውቀት እንዲሻሻልና እንዲለማ እየተሰጡ ያሉ የትምህርት እድሎች አበረታች ናቸው ስራ የሚሰራው በሰው ሀይል ስለሆነ በቀጣይም አማራጮችን በማስፋት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ሲሉም ወይዘሮ ሙሉ ተናግረዋል፡፡ ወቅቱ የሚጠይቀውን የዘመነ አገልግሎት ለመስጠት የሰው ሀይሉ ራሱን በቴክኖሎጂ እንዲያለማና ለመጪው የዲጂታላይዜሽን ዘመን ራሱን እንዲያሰለጥን በየደረጃው የተሰሩት ስራወች ውጤት የተመዘገበባቸው መሆናቸውና ይህንን ተደራሽ በማድረግ በኩል ተግባሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ሃላፊዋ ገልፀዋል፡፡ የሰው ሀይል ስምሪቱ የሜሪት ህጉን ጠብቆ እንዲፈጸም በተደረገው ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር መሻሻሎች መኖራቸውና ቀጣይም የቅደመ መከላከልና የመደበኛ ኢንስፔክሽን ተግባራት ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸው፣ እንደ ሀገር የተደረገው ደመወዝ ማሻሻያ በየደረጃው ያለውን የሰው ሀይል ወደስራ የሚያስገባና መነሳሳትን የፈጠረ በመሆኑ ይህን ምቹ አጋጣሚ ተጠቅሞ በሁሉም ዘርፍ የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ መትጋት እንደሚያስፈልግ በየደረጃው በሁሉም ዘርፍ የመፈጸም አቅምን በማሳደግ ደህንነቱ የተጠበቀ ቀልጣፍና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ወቅቱ የሚፈልገውን የተገልጋይን ርካታ ማረጋገጥ ከመምሪያው እና ከስሩ በሚገኙ አካላቶች የሚጠበቅ ተግባር መሆኑ በውይይቱ የተነሱ ሃሳቦች ናቸው፡፡ በውይይቱ የወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ሲ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት ሀላፊወች፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር ሲ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት ቡድን መሪወች፣ የዞኑ ሲ/ሰ/የሰ/ሀ/ል መምሪያ ጠቅላላ ሰራተኞች እና አጋር አካላት ተገኝተዋል፡፡ በመጨረሻም በመጀመርያው ሩብ ዓመት ወረዳዎች ከተማ አስተዳደሮች እና የመምሪያው ሰራተኞች ማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡