የሰው ሀይሉ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ ስራ ቆጥሮ ሰጥቶ በመቀበል ሂደትና የተሻለ የሰራን በማበረታታት የተገልጋዩን ፍላጎት ማርካት እንደሚገባ ተገለፀ፡

NWCIV:01-11-2025 15:00pm

ወልድያ ፦ ጥቅምት 13/2017 ዓ/ም( ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን) የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ በ2017 ዓ.ም በጀት አመት በለውጥ አተገባበር ስራ ወደ ጎን ከሚያስተዳድራቸው ተቋማት በበጀት አመቱ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን የእውቅናና የማበረታቻ ስርአት ፕሮግራምና የ2018ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት የለውጥ ተግባር አፈጻጸም የዞኑ ስራ አስፈጻሚ፣ የዞኑ ጠቅላላ አመራር እና የዞኑ ቡድን ሸ በተገኙበት ገመገመ፡፡ በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አራጌ ይመር ባለፉት ስኬቶች ለተመዘገቡት የልማት የመልካም አስተደደር እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች ላይ ለተገኙት ስኬቶች እነዚህ የተግባር ማሳለጫ ቁልፎች ያበረከቱት አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከቀጣይ አኳያም ተቋማዊ ጥንካሬ ለመፍጠር በሁሉም ዘርፍ እስከታችኛው መዋቅር ያሉ አደረጃጀቶችን ተጠቅሞ ወደ ስራ እንዲገቡ አቅዶ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡ አጠቃላይ የሰው ሀይሉ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ ስራ ቆጥሮ ሰጥቶ በመቀበል ሂደትና የተሻሉትን በማበረታት አሰራርን ጠብቆ በማስቀጠል ወቅቱ የሚፈልገውን ጠንካራ የድጋፍና ክትትል እስከ-ተጠያቂነት ስርአት መዘርጋት አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡ የሰ/ወ/ዞ/ሲ/ሰ/የሰ/ሀ/ል መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ሙሉ አዲሴ የለውጥ ስራወች የመደበኛ ተግባር ማሳለጫ ሆነው እንዲተገበሩ በ2018ዓ.ም በ1ኛ ሩብ አመት በተደረገው ድጋፍና ክትትል የተሰሩት ስራወች ውጤት የተመዘገበባቸው እና አብዛሀኛወቹ ተቋማት ወደ ተቀራራቢ አፈጻጸም ያመጡ ናቸው ብለዋል። በቀጣይ በጀት አመትም የበለጠ እንዲተገበሩ ከተቀመጠው አሰራር ከፍ ባለ ደረጃ ወጥና ጠንካራ የሆነ የክትትልና የድጋፍ ስርአት በመዘርጋት የተቋማትን የመፈጸም አቅም ማሳደግ ላይ ተግተን እንሰራለን ሲሉ ወ/ሮ ሙሉ ገልፀዋል፡፡ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ዞናችን ያለበትን ሁኔታ ስንመለከት በበርካታ ዘርፎች ህዝብን አርክተናል ማለት አይቻልም ባለን ክትትልም ይህንኑ አረጋግጠናል እነዚህን መሰረታዊ ክፍተቶች አርመን ቀጣይ ወደ ተሻለ የአፈጻጸም ቁመና ለመግባት ከወቅቱ ጋር የሚሄድ ዘመናዊ አሰራርን ለመከተል የተጀማመሩ ስራወችን ይበልጥ አጠናክረን በማስቀጠል ችግሮቹን ለመሻገር እንጥራለንም ብለዋል። ከተሳታፊዎችም ከመንግስት ሰራተኛው አኳያ የነበረውን የኑሮ ማሻሻያ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ እንደ መንግስት በተጠና፣ በተደራጀና በፈጠነ መልኩ ምላሽ ተሰጥቷል። ይህንን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የሰው ሀይሉ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ በየደረጃው ያለው አመራር በስራ ማረጋገጥ አለበት የሀገራዊ ሪፎርም አተገባበር ስራወች መሬት እንዲነኩ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ በየደረጃው ያለውን የሰው ሀይል በእውቀት፣ በቴክኖሎጂ እንዲለማና እንዲበለጽግ እንደመምሪያችን የተለያዩ ስልጠናወችን እየሰጠን ነው፤ እንደ-ሀገር የሰው ሀይሉ በኮደርስ እንዲሰለጥን የመጡት እድሎችም የሚደነቁ ሆነው ሌሎች ተጨማሪ አማራጮችን በማስፋትም ሰው ሀይል ልማት ላይ መሰራት እንዳለበት በውይይቱ የተነሱ ሃሳቦች ናቸው፡፡ በመጨረሻም ሲቪል ሰርቪስ መምሪያው ከለውጥ ተግባራት ጋር በተያያዘ ወደ ጎን የሚያስተዳድራቸውን ተቋማት ባደረገው አመታዊ ምዘና ከተካሄደባቸው 33 የዞን ተቋማት በሪፎርም(በለውጥ) ስራ በተቋማት አያያዝ እና አሰራር መመሪያ ተመዝነው ብልጫ ላመጡ የዞን መምሪያዎች የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡